የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፍነው አርብ በተካሄደው የግብፅ እና ኢትዮጵያ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ቅሬታ እንዳለው ለፊፋ አሳውቋል።
ፌዴሬሽኑ ሁለት ጉዳዮች ላይ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል። የመጀመሪያው ከተመልካች ይለቀቅ የነበረ አብረቅራቂ ተንቀሳቃሽ መብራት ተጫዋቾች ላይ ተፅእኖ ፈጥሯል ብሏል።
በተለይ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ፍፁም ቅጣት ምቶች ሲመቱበት ትኩረቱን እንዲያጣ እንዳደረገው የፌዴሬሽኑ ቅሬታ ያሳይል። ሁለተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር የተጋጣሚ ደጋፊዎች ክብር በጎደለው መልኩ ሲጮሁ ነበር ብሏል ፌዴሬሽኑ።
እነዚህ ሁለት ጉዳዮች የፊፋን የስነምግባር መተዳደሪያ ደንብ የሚጥሱ በመሆናቸው ተቋሙ ጉዳዩን መርምሮ አስፈላጊውን ቅጣት እንዲያስተላልፍ ፌዴሬሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።
በሸዋንግዛው ግርማ