በሀገሪቱ በየዘርፋ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በሀገሪቱ በየዘርፋ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት መሆኑ ተገለፀ

AMN – ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም

በሀገሪቱ በየዘርፋ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለፁ።

ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን በሳይንስ ሙዚየም “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ ቀኑ በሀገሪቱ ባለፉት ሰባት አመታት የተመዘገቡ ሁለንተናዊ ስኬቶች እና ድሎች የሚቃኙበት ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የማእድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የተለያዩ ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታዎች፥ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ባለፋት ሰባት አመታት ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ ስራዎች አስተማማኝና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት አስችለዋል፡፡

በዚህም ቁልፍ የልማት ዘርፎች በሆኑት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች ዘርፎች ተጨባጭ እድገት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡ እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦች ኢትዮጵያ በቀጣይ ጥቂት አመታት የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክቱ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በሀገሪቱ የተሟላ የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ መደረጉ በዘርፋ የሚታዩ በተለይም የዋጋ ግሽበትን፣ የውጭ ምንዛሪ መዛባትንና አቅርቦት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑበት ነው። በዚህም ለእመርታችን መሠረት የሆኑ መልካም ውጤቶችን እየተመለከትን ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review