ከጎንደር ከተማ የተውጣጡ እንግዶች የአምቦ እና ወንጪ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

You are currently viewing ከጎንደር ከተማ የተውጣጡ እንግዶች የአምቦ እና ወንጪ የልማት ስራዎችን ጎበኙ
  • Post category:ልማት

AMN ጳጉሜን 3/2017

ከጎንደር ከተማ የተወጣጡ እንግዶች የአምቦ እና ወንጪ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የጎንደር ከተማ የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና እና ወንጌላውያን እምነት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ ኅብረተሰተብ ክፍል ተወካዮች የአምቦ ከተማ የኮሪደር ልማት፣ ታሪካዊቷን የደብረ ገነት ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም፣ የወንጪና ደንዲን ኤኮ-ቱሪዝም ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

በጉብኝቱም የጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌችና የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ አካላት የታሪካዊቷን ገዳም የሙዝየምና ተያያዥ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።

የጎንደር እንግዶች በታሪካዊቷ ገዳም ያደረጉት ጉብኝትም የኢትዮጵያውያን ትስስር የማይበጠስና ከጥንተ ታሪክ እንደሚመነጭ የቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ሕያው ምስክር መሆኗም ተገልጿል።

የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው በዚሁ ወቅት በአምቦና ወንጪ አካባቢ ሲደርሱ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

በታሪካዊቷ የቂርቆስ ገዳም ጉብኝታቸውም በጎንደርና ወንጪ መካከል ከ400 ዓመታት በፊት በአፄ ፋሲለደስ ዘመን የተከናወነ አስደናቂ ተግባር ማየታችን አስደንቆናል ማለታዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review