‎‎አዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ተመራጭ ዘመናዊ ከተማ እየሆነች መምጣቷን የፕላንና ልማት ቢሮ ገለጸ

You are currently viewing ‎‎አዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ተመራጭ ዘመናዊ ከተማ እየሆነች መምጣቷን የፕላንና ልማት ቢሮ ገለጸ

AMN – ጳጉሜን 03/2017 ዓ.ም

‎አዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ በማምጣት የማንሰራራት ዘመንን የሚያበስር፣ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ተመራጭ ዘመናዊ ከተማ እየሆነች መምጣቷን የከተማና ፕላንና ልማት ቢሮ ገልጿል።

‎የቢሮው ሀላፊ አቶ አደም ኑሪ፣ ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀንን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። መዲናዋ ዓለም አቀፋዊ ስታንዳርድ በመያዝ ተወዳዳሪ ካደረጓት ስልቶች መካከል 30፣30፣40 የሚለውን የከተማ ፕላን ምጣኔ ህግን በተቀናጀ አካሄድ ተግባራዊ እያደረገች በመገኘቷ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‎30 በመቶ የአረንጓዴ፣ 30 በመቶ የመንገድ እና‎ የ40 በመቶው የግንባታ እና ተያያዠ የከተማ ፕላን ምጣኔ ድርሻ በአግባቡ በመተግበር የከተዋን የማንሰራራት ጉዞ ማቀላጠፍ ተችሏል ብለዋል፡፡

‎የኮሪደር ልማት ስራው ለመዲናዋ ነዋሪዎች ፍትኃዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የህጻናት መጫዎቻዎችን በማመቻቸት፣ የመዝናኛና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን በመገንባት፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን፣ ፓርኮችን በመስጠት የከተማዋን ነዋሪዎች ፋላጎት ማሟላት እንደተቻለም ነው የቢሮ ሀላፊው የገለጹት፡፡

‎በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሀብታዊ፣ በሰው ተኮር ተግባራት፣ አገልግሎቶችን በማዘመን እና ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በተቀናጀ ስትራቴጂ በመተግበር የሚታዩ ውጤቶች ስለመመዝገባቸው አመላክተዋል፡፡ የተቋም ግንባታ፣ ምቹ የስራ አካባቢ ውጤታማ በማድረግ እንዲሁ የከተማዋን ስማርት ሲቲ ግንባታ ለማጠናከርና አገልግሎትን በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ ለውጦች መምጣታቸውንም ገልጸዋል።

‎ከሪፎርም በኋላ የስራ ክፍሎች እንደ ባህሪያቸው መደራጀታቸው የተገልጋይ እርካታ እንዲሻሻል ተደርጓል ያሉት አቶ አደም፤ ከአሰራር አንጻር ግልጸኝነት ያላቸው አዋጆች፣ ደንቦች፣ የአፈጻጸም መመሪያዎች ተዘጋጅተው በመተግበራቸው በተቋማት የስራ አፈጻጸም ላይ ውጤቶች ማየት ተችሏል፡፡ ‎አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት በመጪው መስከረም ሥራ እንደሚጀምርም አቶ አደም ኑሪ ተናግረዋል።

‎የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በከተማዋ ዋና ዋና መግቢያ በሮች የገበያ ማዕከላትን በመገንባትና በእሁድ ገበያ አምራቹና ገዥው በቀጥታ እንዲገናኝ ተደርጓል ብለዋል። የትውልድና የአገር ግንባታ ምሰሶ በሆነው የቀዳማይ ልጅነት እድገት ፕሮግራም፣ የከተማችን 1.3 ሚሊዮን ህጻናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።፡ በ26 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት የማይችሉ 36,600 ዜጎች የምገባ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

በሄለን ጀንበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review