AMN- ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም
በነሀሴ ወር መጨረሻ አዲስ አመት ከሚጀምርበት መስከረም አስቀድመው የሚገኙ ጥቂት ቀናት የያዘች ናት ጳጉሜን።
ይችህ ወር ለኢትዮጰያውያን አንድ የአሮጌ አመት መዝጊያ እና የአዲስ አመት መጀመሪያ መሆኑን ተከትሎ ሰዎች ራሳቸውን የሚገመግሙበት ከመሆኑ ባሻገር ለመጪው አመት መልካሙን የሚያቅዱበት ነው ። ይህ ሁኔታም ኢትዮጰያን ከአለም የተለየ ከሚያደርጓት ጉዳዮች ውስጥ የራሷ የዘመን አቆጣጠር ባለቤት በመሆኗ ነው ።
የዘመን አቆጣጠሩ የተለየ የሚያደርገው ደግሞ 13 ወራት ወይም ተጨማሪ የጳጉሜን ቀናት ባለቤት በመሆኗ ልዩ ያደርጋታል። የጳጉሜ ቀናት የዘመን ወለወጫ መሸጋገርያ ናት ። ኢትዮጰያውያን በአመቱ ማብቂያ ያለፈውን አካሄዳቸውን የሚፈትሹበት ለአዲሱ አመት የሚያቅዱበት ወር ጰጉሜን ናት።
ኤ ኤ ኤን ዲጅታል ወርሀ ጳጉሜን አስመልክቶ ከውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ፣ ስለ አምስቱ የጳጉሜን ቀናትን ከተቋማቸው ተልዕኮ አኳያ ቆይታ አድርገዋል ። የኢትዮጰያ የዘመን አቆጣጠር 13ኛዋ ወር ላይ እንደ ሀገር ሰከን ብለን ፣ቆም ብለን ያለፍንበትን ግዜ የምናስበበት ወቅት ነው ያሉት ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ። በእነዚህ ቀናት ለቀጣይ አመት እቅድ የምናቅድበት መሸጋገርያ መሆኗን ፣ እያንዳንዱ ቀናት የራሱ ትርጉም እንዳለው የገለፁት ሚንስትሩ ናቸው።
ጳጉሜን አንድ የጽናት ቀን ፅናት ማለት አንድን ነገር ለማሳካት ወይም አንድን ሁኔታ ለመቋቋም ጠንክሮ መሥራት እና ተስፋ አለመቁረጥ ማለት ነው። ፅናት (መቋቋም) ማለት ከችግሮች የማገገም ችሎታ ማለት ነው። ኢትዮጰያም አሳሪ ችግሮቾን ተቋቁማ የማለፍ ጥበቧ ከጊዜ ወደ ግዜ ከፍ ማለት መጀመሩን በቂ ማሳያዎች አሉ ። በአገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ዘርፎች የተገኙት ውጤቶች በፅናት በጋራ መቆም ስለቻልን ነው በማለት ኢንጅነር ሀብታሙ (ዶ/ር)፣ የተናገሩ ሲሆን ውጤቱን ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ መፅናት ያስፈልጋል ነው ያሉት ።
ለአብነትም ሀገራቸውን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በገደል በሀሩሩ የሚወድቁላት ጀግና እና ፅናት ያነገቡ የመከላከያ ሰራዊቶችን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ። ጳጉሜን ሁለት የህብር ቀን ኢትዮጰያ በብዙ መንገድ ህብረብሄራዊነት የሚገልፁ እና በጋራ የምንቆምላቸው ጉዳይ የምናሳካቸው ጉዳዮች አሉን። የህብር ቀንን ከህዳሴ ግድብ አኳያ በጋራ ሆነን የሰራንበት ትልቅ አሻራችን ነው የሚሉት ሚንስትሩ፣የጋራ ሀብቶቻችን የትውልድ የሚቀመጥ አሻራችን ወይም ሀውልታችን ነው ሲሉ ይገልፃሉ።
በህብረ ብሔራዊነታችን የምናስቀጠላት አገር ናት ኢትዮጰያ። የተለያየ ብሔር ማንነት ቋንቋ ያለን ኢትዮጰያውያን ጳጉሜን ሁለት ላይ ተምናስብበት ቀን ነው ብለዋል። ጳጉሜን ሶስት – የእምርታ ቀን እንደ ሀገር ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል። ውሀ እና ኢነርጂ ሚንስቴር 2017 በጀት አመትም ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን ሚኒስቴሩ ያነሳሉ ። በሶስት ዋና ዋና ምሶሶዎች ማለትም መጠጥ ውሀ እና የንፅህና አጠባበቅ ላይ በሌለ ሀብት ዜጎችን በማነቃነቅ ለውጦች ያመጣንበት አመት ነው ብለዋል።
ከ4 ሚሊዮን ዜጎች በላይ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው፣ጠቅላላው ከተሰራው ጋር ሲደመር 76 ሚሊዮን የመጠጥ ውሀ እንዲያገኙ መደረጉንና ፣ በንፅህና አጠባበቅ ዙሪያ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ። ይህ እንደ ተቋም ትልቅ እምርታ መሆኑን አስረድተው፣ ከተማዎችን የማዘመን እና ንፁህ የማድረግ ስራ ሌላኛው የተሰራው መሆኑን አንስተዋል።
ከተሞች ንፁህ እና ሳቢ እንዲሆኑ የንፅህና አጠባበቅ ፕሮግራም በ22 ከተሞች ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። በተለይ ጋምቤላ ፣ ሰመራ ፣ ጎንደር ፣ ነቀምት፣ ጂማ ፣ሻሸመኔ ፣ ሀረር ጨምሮ በ14 ከተሞች የፍሳሽ ማጣሪያ ልማት መሰራቱን ተናግረዋል ። እንዲሁም በሀዋሳ በባህር ዳር በድሬዳዋ እና አዳማ ጨምሮ በስምንት ከተማሞች ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
በተለይም ከከተማ ራቅ ብለው ለሚኖሩ ዜጎችን ህይወት ለማሻሻል ኦፍ ግሪድ ቴክኖሎጂ ወይም በሶላር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራቱን እና በዚህም በጠቅላላው የዝርጋታው መጠን 54 በመቶ ማድረስ መቻሉን ሚንስትሩ ገልፀዋል። ከተጠቃሚዎች አንፃር 10ሺህ የሚደርሱ ዜጎች የሶላር ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ፣ 22 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ኢነርጂ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ማድረስ መቻሉን አብራርተዋል ። የውሀ ሀብት አስተዳደር አንዱ የዘርፉ ተልዕኮ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ የውሀ ፖሊስያችን ውህ ሳይባክን እንዲቆይ ማድረግ ነው ፡፡
ስለሆነም ለተግባራዊነቱ በትኩረት እና በቅንጅት እየተሰራበት መሆኑንና የተፋሰሶች ምክር ቤት አዋጅ ሁሉም ክልሎች አባል የሆኑበት አሰራር መዘጋጀቱን ጠቁመዋል ። የውሀ ሀብቶቻችን እንዳይበላሹ፣ እንዳይባክኑ እና እንዳይጎዱ በሕግ የመደገፍ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል። እነዚህን ስራዎች መለስ ብለን ስናይ ከፍተኛ እምርታ ያገኘንበት ነው በማለት ያስረዳሉ።
የጳጉሜን አራት የማንሰራራት ቀን ኢትዮጰያ ለአመታት እንደዘፈኖቿ እንዳልነበረች ያስታወሱት ሚኒስትሩ ፣ መሬት እየተራቆተች ፣ምንጮች እየነጠፉ እና ድርቅ የበዛባት ሀገር ሆና ዘልቃለች ።
ኢትዮጰያን በማልበስ ንቅናቄ እንደ ሀገር ማንሰራራት መጀመሩን ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ያነሱት ሚንሰትሩ፣ ለተከታታይ ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመተግበሩ እየተመናመነችና እየተራቆተች የወጣችው አገር መልሳ ስጋ እና ደም እንዲኖራት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።
አረንጓዴ አሻራን ችግኝ መትከል አይደለም ካሉ በኋላ ችግኝ በመትከል ውስጥ ቡና ፣ አቮካዶ፣ማንጎ እና ሌሎችም ፍራፍሬዎች እንዳሉ ገልፀው፣ በተለይ በዘንድሮ በጀት አመት የቡና ኤክስፖርት አቅም ማደጉንና የቡና ኤክስፖርት በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት ሁኔታ መፈጠሩን በኢኮኖሚ የማንሰራራት የተጀመረበት መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የአቮካዶ እና የፍራፍሬ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጰያ ውስጥ አቮካዶ የሚበላው በአንዳድ አከባቢዎች ብቻ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ላይ ፕሮሰስ ወደ ማድረግ አድጎ ለውጭ አገሮች ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ፣ በርካታ ወጣቶችም በዘርፉ ተሰማርተውበት ተጠቃሚ መሆናቸውንም አንስተዋል።
በአረንጓዴ አሻራ በተሰሩ ስራዎች ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ እና የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ያነሱት ሚኒስትሩ ፣ በስንዴ ላይ የመጣው ለውጥ ራስ እስከመቻል የተደረሰው የኢትዮጰያን ከፍታ ጉዞ የተጀመረት እንደሆነ አስረድተዋል። የጳጉሜን አምስት የነገ ቀን ጳጉሜ አምስት የመሸጋገሪያ ቀን መሆኗን የሚገልፁት ሚንስትሩ፣ ዛሬ ላይ ቆመን ትላንት ላይ ያመጣነውን ስኬት የምናስቀጠልበት ነው በማለት ገልፀዋል። ነገ ለምናደርጋቸው ጉዞ ከትላንቱ ልምድ ውስደን ለነገ ስንቅ የምናስብበት ቀን ነው በማለት ገልፀዋል ።
በሔለን ተስፋዬ