አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ
  • Post category:አፍሪካ

AMN – ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ መርሃግብር አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው በመግለፅ ከፍተዋል።

እንደ አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ ግብርና እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማውሳትም የኢትዮጵያን ሥራዎች በምሳሌነት በማንሳት አውስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ በመግለጽ Climate Innovation Compact የተሠኘ በ2030 1ሺ አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።

አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ የመምራት አቅሟንም በማጽናት አንስተዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የCOP32 ጉባኤን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም አቅርበዋል።

ይኽም ሀገራችንን እና አኅጉራችንን በአየርንብረት ጥበቃ ተግባር የመሪነት ሚና የሚያጎናፅፍ እንደሚሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review