ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት ቴሬሳ ሪቤራ ጋር በተለያዩ የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸዉን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ከአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት ቴሬሳ ሪቤራ ጋር ተገናኝተን በተለያዩ የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡