የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአይበገሬነታችን ምልክት ለሆነዉ ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን ምረቃ እንኳን አደረሰን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የፅናታቻን ፣ የላባችን ፣ የደማችን ፣ የጥረታችን ዉጤት ፣ የዘመናት ቁጭታችን መደምደሚያ ፣ የብልፅግናችን መሰረት ፣ የአይበገሬነታችን ምልክት ለሆነዉ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን ምረቃ እንኳን አደረሰን ብለዋል፡፡
ባንድነት ስንቆምና ስንተባበር የማችለዉም የለም በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡: