ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአባል ልጆችን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ታዬ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የማደግ መሻት በላባቸው፣ በእንባቸው፣ በደማቸው እና በክብራቸው ያሳኩት ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ህዳሴ ግድብ የአባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የኢትዮጵያ የቀጣይ ጊዜ ታላላቅ ስኬቶች ጅማሮ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
#Ethiopia
# Dam