ህዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ፤ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

You are currently viewing ህዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ፤ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ

‎AMN – ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም

‎ህዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ፤ የመጪው ንጋት ማብሰሪያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ከመጡ የአገር መሪዎች ጋር በይፋ መርቀዋል። በምርቃት ወቅት ባደረጉት ንግግር ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።

‎ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ እንችላለን፣ እንቀጥላለን፣ ማለት ትችሉ ዘንድ ግድቡን መጥታችሁ እንድትጎበኙ በማለት ጋብዘዋል። ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ዘር ታሪክ የመጀመሪያው ታላቅ ስራ መሆኑን ተናግረዋል። ህዳሴ ትውልድ የሰራው ገድል መሆኑን፤ ታሪክ ከመስማት አልፈን ታሪክ ሰርተን ለማውራት በቅተናል ብለዋል።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review