ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚገድባቸው አንዳችም ምድራዊ ሐይል እንደሌለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚገድባቸው አንዳችም ምድራዊ ሐይል እንደሌለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ

AMN – ጳጉሜን 4/2ዐ17 ዓ.ም

ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚገድባቸው አንዳችም ምድራዊ ሐይል እንደሌለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ድኤታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር/ኢ/ር) ገለፁ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መልዕክት የማንሰራራት ቀንን ከተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በጋር በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ጥቅማችን ለማስከበር የሚገድብ ምንም አይነት ምድራዊ ሐይል አለመኖሩን ማሳያ ነው ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ድኤታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር/ኢ/ር) ገልጸዋል።

ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ገናናነት በነበር ያስቀየረ እና የዚህ ዘመን ድል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮችና ሴክተሮች ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ ናቸው።

ሀገራት ወደ ማንሰራራት ሲጓዙ ጠንካራ ፈተና የበዛበት መንገድ ይገጥማቸዋል፣ ሁሌም በማንሰራራት ጉዞ ውስጥ መንግስት እና ሕዝብ በጋራ ሲሰሩ የማይታለፍ ፈተና የለም፤ በጠነከርን ቁጥር የሚገጥሙ ፈተናዎችን ለመመከት በጋራ በመቆም በጋራ በመመከት አለብን ብለዋል አቶ አክሊሉ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጡ ባለሙያዎች እና እንግዶች አሁን ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ስነ ስርዓት በቀጥታ እየተከታተሉ ሲሆን፣ የተመረጡ የአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review