አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እየተወጣ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እየተወጣ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

AMN – ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እየተወጣ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልፀዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የዘመን መለወጫን አስመልክቶ ለሚያስተምራቸው ልጆችና ለወላጆች ማእድ አጋርቷል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በመርሃ ግብሩ ወቅት ኢትዮጵያውያን መተባበርና መደጋገፍ ባህላችን ነው፤ ለዚህም ተጠናቆ ለምርቃት የበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ እንደ ሚዲያ የመረጃ ድልድይ ከመሆን ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም ገልፀዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በየጊዜው እራሱን እያዘመነ ትውልድ ግንባታ ላይ የላቀ አበርክቶ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ካሳሁን፤ የተጀመሩ ማህበራዊ አገልግሎት ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

ኤ አም ኤን የትውልድ ድምጽነቱን ይበልጥ ለማረጋገጥ በሚያከናውነው ስራ በሐገር ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል ያሉት አቶ ካሳሁን፤ አሁንም ዘመኑን በሚመጥን አግባብ ራሱን አደራጅቶ ወደ ህዝብ እየቀረበ ነው ብለዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት በበኩላቸው ሚዲያው ከተቋቋመለት መደበኛ ተልእኮ ባሻገር አለኝታነቱን ስላሳያቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ምስጋናን አቅርበዋል።

በመረሐ ግብሩ ለተማሪዎችና ለተማሪ ወላጆች የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review