የአዲስ አበባ ከተማ የምክትል ከንቲባ ቢሮ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለሰራተኞቹ ማዕድ አጋርቷል።
ማዕዱን ያጋሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ ሁልጊዜ ዘመን ከዘመን ሲሸጋገርና በዓላት ሲመጡ ያገኘነውን በበጎነት ተካፍለን መጠቀም ባህል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቅ የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ለኢትዮጵያውያን የተለየ ያደርገዋል ሲሉ አቶ ጃንጥራር ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የምክትል ከንቲባ ቢሮ ሰራተኞችም ለተደረገላቸው የማዕድ መጋራት አመስግነዋል።
በንጉሱ በቃሉ