በመዲናዋ የተከፈቱ 20 ባዛሮችን ጨምሮ በ219 ቅዳሜና እሁድ ገበያ እና 5ቱም ገበያ ማዕከላት በቂ ምርት እየገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ አስታዉቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቢሮው ከኦሮሚያ ክልል ጋር በፈጠረዉ የገበያ ትስስር ተጨማሪ የግብርና ምርቶች ወደ መዲናዋ እየገቡ ነዉ፡፡
ከዘመን መለወጫና ሌሎች በአላት በዓል ጋር በተያያዘ 219 የቅዳሜና እሁድ ገበያ ፤ አምስት የገበያ ማዕከላት እና 20 ባዛሮች በመዲናዋ መከፈታቸዉን ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ገልጸዋል፡፡
ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተፈጠረዉ በዚህ የገበያ ትስስር የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ የእንስሳት ተዋፅኦዎችና ሌሎች የበአል ምርቶች በቂ ሁኔታ እየገቡ መሆናቸዉን የአዲስ አአባ ከተማ አስተዳድር ንግድ ቢሮ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡