ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሳካት ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለፀ

You are currently viewing ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሳካት ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለፀ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም

እንደ ህዳሴ ግድብ አይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሳካት ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ2017 እቅድ አፈጻጸምና የ2018 እቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በተጠናቀቀው የ2017 ዓ.ም ከህዝባዊ መድረኮች፤ ከተቋማትና ከግለሰቦች ውጤታማ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከአገር ውስጥ ባለፈ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር እንዲሳተፉ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህም በቅርቡ በሰሜን አሜሪካና በካናዳ የተደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ግልጽና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን አንስተዋል።

እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ገለጻ፣ እንደ ህዳሴ ግድብ አይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሳካት ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለማራመድ አለመግባባቶችን በምክክር መፍታት ይገባል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ችግሮችን ለመፍታት ከውይይት ውጪ አማራጭ አለመኖሩን በመረዳት ለውጤታማነቱ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review