ያለፈው ዓመት የግድባችንን ፍፃሜ አብስሮ፣ በሁሉም ያቀድናቸው ተግባራት የነበረን አፈፃፀም መልካም ሆኖ አልፏል። የሚገባንን ያህል ባይሆንም የምንችለውን ያህል ሠርተንበታል። የሚቀረን ቢኖርም ታላላቅ ስኬቶችን አግኝተንበታል።
ከዛሬ ነገ ይበልጣል። ያልተነካ ብዙ ሀብት አለው። እኛም ከትናንት የተማርነው ብዙ ልምድ አለን። ያካበትነው ብዙ ወረት አለን። ነገ ከትናንት የበለጡ ታላላቅ ዕቅዶች ከፊታችን አሉ።
እነዚህ ዕቅዶች ሲፈፀሙ የትናንትናዋን ኢትዮጵያ ከነገዋ ኢትዮጵያ የሚለዩ ናቸው። የኢትዮጵያን ማንሠራራት መሠረት አስይዘው ብልጽግናችንን ይበልጥ የሚያረጋግጡ ናቸው።
ኢትዮጵያን የምንወድ ሁሉ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በጋራ እንትጋ፣ ውጤታማ እንሁን፣ ታሪክ እንስራ።
መልካም አዲስ ዓመት፤ መልካም የሥራ ዓመት ይሁንልን።