በኦሮሚያ ክልል የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ገለጹ።
በክልሉ ሸገር ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመር የሚያስችል የምረቃ መረቃ መርሃ ግብር ተከናውኗል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ በክልሉ የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ዛሬ ከሸገር በተጨማሪ በአዳማ፤ ሻሸመኔ፤ ቢሾፍቱ እና ጅማ ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ለመጀመር የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን የአገልግሎት ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተው አሰራርን ዘመናዊ ፈጣንና ቀልጣ የማድረስ ስራ በልዩ ትኩረት በሁሉም አካባቢዎች የሚቀጥል መሆኑንም አረጋግጠዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፤ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት ለመጀመር ቀደም ብሎ ዝግጅት መደረጉን አስታውሰው አሁን ላይ የተሟላ ዝግጅት ተደርጎ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዚህም በተቋማት የህዝብን የመገልገል ፍላጎት በተሟላ መልኩ ምላሽ ለመስጠት የተቀናጀ ጥረት ይደረጋል ሲሉ መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በማእከሉ አገልገሎት ለመስጠት ከተገኙት ሰራተኞች መካከል አቶ አለማየሁ ታፈሰ፤ ለህዝባችን ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡