ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ ከተቀመጠለት ጊዜ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለፈበትን ሁኔታ የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሠረት ድንጋይ ከተቀመጠለት ጊዜ ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለፈበትን ሁኔታ የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል

AMN-መስከረም 03/2018 ዓ.ም

“ኢትዮጵያ ትችላለች” በሚል መሪ ቃል የታላቁን ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተከፍቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አስመልክቶ በከተማ ደረጃ በማዘጋጀት የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ለእይታ ክፍት አድርጓል።

በዚህ በተዘጋጀዉ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

📷 መባፂዮን ሃ/ገብረኤል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review