ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝቡን የሠላሙ ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ሠላም ዘላቂና አስተማማኝ ማድረግ መቻሉን ተናገሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ህዝቡን የሠላሙ ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ሠላም ዘላቂና አስተማማኝ ማድረግ መቻሉን ተናገሩ

AMN – መስከረም 3/2018 ዓ/ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቅርብ አመታት ወዲህ ህዝቡን የሠላሙ ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ሠላም ዘላቂና አስተማማኝ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ የከተማዋን ደህንነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የሠላም ሠራዊት አደረጃጀቶች ተፈጥረው ወደ ሥራ እንዲገባም ተደርጓል ብለዋል፡፡

ከተማዋን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ ዕቅዶች በበዙበት ጊዜ በፀጥታ አካላት ብቻ በሚሰራው ሥራ የአዲስ አበባን ከተማ ሠላም ዘላቂና አስተማማኝ ማድረግ እንደማይቻል በመረዳት ህዝቡ የአካባቢውን ሠላም እንዲጠብቅ የብሎክ አደረጃጀቶችን መፈጠር መቻሉን ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

ለተፈጠረው አደረጀጀት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ለፀጥታ አካላት መረጃና ጥቆማ የመስጠት ስራዎችን እንዲሰራ የተደረገ ሲሆን፤ የፀጥታ ቢሮም የክትትልና ድጋፍ ተግባራትን ያከናውናል ብለዋል፡፡

ከህብረተሰቡ ውስጥ የተወጣጡ 2 ሺህ 75 የሰላም ሠራዊት መኖሩን ገልፀው፤ የሠላም ሠራዊቱ ከህብረተሰቡ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሠራቱ የከተማዋን ሰላም ዘላቂ እና አስተማማኝ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል፡፡

በበረከት ጌታቸዉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review