ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚህ ትዉልድ የመቻል ማሳያ እና የአርበኝነት ምልክት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለፁ፡፡
ቢሮዉ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን ተከትሎ የስፖርት ፌስቲቫል እና የጎዳና ላይ ትርዒት አካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የህዳሴ ግድብ የዚህ ዘመን ወጣት አሻራ የተገለጠበት ዳግም አድዋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ የህብረት እና የትብብር ዉጤት ማሳያ እንዲሁም የተገኘው ትምህርት ዘርፈ ብዙ ነዉ ያሉት አቶ በላይ፤ ለኢትዮጵያዊያኑ የጋራ ቤት ለሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችም መልዕክቱ የላቀ ነዉ ብለዋል፡፡
ህዳሴ ግድብ የወጣቶችን መነሳሳት በልማት ለመግለጥ ስንቅ የሚሆን ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
በተመስገን ይመር