ከንቲባ አዳነች አቤቤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በተመለከተ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ያለውን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮዽያ ችላለች፤ ኢትዮዽያ የድል አድራጊዎች ፣ የአሸናፊዎች ምድር መሆኗን ጠቅሰዋል።
መላዉ አዲስ አበባ ለዳግማዊዉ የአድዋ ታላቅ ድል ክብር ከሌሊት አንስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በከፍተኛ የድል አድራጊነት ስሜት በነቂስ እየተመመ እንደሚገኝም ነው ከንቲባ አዳነች በመልዕክታቸው የጠቀሱት።