በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።
አትሌት ትዕግስት ከኬንያዊቷ አትሌት ፒርስ ጅፕችርችር ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጋ ነው የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ ያስገኘችው።
በሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ትዕግስት አሰፋ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 24 ደቂቃ 45 ሰከንድ ወስዶባታል።
ከኬንያዊቷ ፔርስ ጄፕቼርቺር ጋር እስከ መጨረሻው የተፎካከረቸው ትዕግስት፤ ውድድሩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሜትሮች ሲቀሩ በኬንያዊቷ አትሌት ተቀድማለች።
በፓሪስ ኦሎምፒክ ተመሳሳይ የብር ሜዳልያ ያገኘችው ትዕግስት አሰፋ፤ በቶክዮ ውድድር ከጉዳፍ በመቀጠል ለሀገሯ ሁለተኛውን ሜዳልያ አምጥታለች።