የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሃገራዊ ልማቶች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሃገራዊ ልማቶች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

AMN – መስከረም 4/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሃገራዊ ልማቶች የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቋል፡፡

ምክር ቤቱ የ2017 የመጅሊስ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋናና እውቅና መርሀ ግብር አካሂዷል።

የምርጫዉ ሂደት ዲሞክራሲያዊና ሁሉንም አካላት ያሳተፈ እንዲሆን በርካታ አካላት ሚናቸውን ተወጥተዋል ያሉት በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የ2017 የመጅሊስ ምርጫ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በቀጣይም በሃገራዊ ልማቶች ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ ተናገረዋል፡፡

የ2017 ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review