በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ተምህርት ቤቶች የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር መርሀ ግብር ተጀመረ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ተምህርት ቤቶች የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር መርሀ ግብር ተጀመረ

AMN መስከረም 5/2018

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በዱዱቢሳ ቅድመ አንደኛና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የመማር ማስተማር ሂደቱን አስጀምረዋል።

ተማሪዎችና መምህራንን ጨምሮ ሁሉም የትምህርት ቤት አስተዳደር በተገኙበት በተሟላ ግብዓት የመማር ማስተማሩን ሂደት አስጀምረዋል።

በትምህርት የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ግብዓት ቀድመው ላልወሰዱ ተማሪዎች ቁሳቁስ የተሰጠ ሲሆን የምገባ መርሀ ግብሩም ተጀምሯል።

የ2018 የትምህርት ዘመንን ውጤታማ ለማድረግም ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታዉቋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review