ለ2018 የትምህርት ዘመን ከአምናው በተሻለ የትምህርት ግብአቶችን ተደራሽ ስለማድረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገለጸ

You are currently viewing ለ2018 የትምህርት ዘመን ከአምናው በተሻለ የትምህርት ግብአቶችን ተደራሽ ስለማድረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ገለጸ

AMN – መስከረም 5/2018 ዓ.ም

ለ2018 የትምህርት ዘመን ከአምናው በተሻለ የትምህርት ግብአቶችን ተደራሽ ስለማድረጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ከኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከተማ አስተዳዳሩ ባለፉት አምስት አመታት ከደንብ ልብስ ጀምሮ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንና ይህም ለትምህርት ውጤታማነት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል፡፡

በግብዓት አቅርቦት ከዚህ ቀድም የወራት መዘግየቶች እንደነበሩ አስታውሰው፤ በተለይ ከመጽሐፍት አቅርቦትና ከደንብ ልብስ ጋር በተያያዘ፣ ከዚህ ቀደም የሚስተዋሉ መዘግየቶችን ለመፍታት ታስቦ ከነሐሴ ወር ጀምሮ የመጽሃፍት ስርጭት ስለመካሄዱም አብራርተዋል፡፡

በሁሉም የትምህርት አይነቶች ካለፈው አመት ጀምሮ የመጽሃፍት ስርጭት አንድ ለአንድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለግል ትምህርት ቤቶችም መጽሐፍት በሽያጭ እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡

እስካሁን ባለው ሂደትም ትምህርት ቤቶቹ በጊዜ መጽሐፍት በመግዛት ለተማሪ እንዲያከፋፍሉ በተደረገው ጥረት የገዙ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አንስተው፤ ያልገዙ ትምህርት ቤቶችም አስቀድመው በመግዛት ለትምህርት ጥራት መጠበቅ እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

እንደ መጽሃፍት ያሉ የትምህርት ግብአቶችን በአግባቡ በመያዝ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን እንዲያገለግሉ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በረውዳ ሸምሱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review