ባለስልጣኑ የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ ገንብቶ በማጠናቀቅ የምርቃት ፕሮግራም አካሄደ

You are currently viewing ባለስልጣኑ የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ ገንብቶ በማጠናቀቅ የምርቃት ፕሮግራም አካሄደ

AMN – መስከረም 6/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያስገነባውን የድምፅ እና የምስል ስቱዲዮ በማጠናቀቅ የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የምርቃት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፤ የስቶዲዮ ግንባታው ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት በከተማችን የደንብ ጥሰት እንዳይፈጽም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎቻችን በማጠናከር ህብረተሰቡ ህገወጥነትን እንዲጸየፍ በሚዲያ ስራውን ለማጠናከር መሆኑ መግለፃቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋሙ የገጽታ ግንባታ ስራውን አጠናክሮ በመስራቱ በየጊዜው የሚታይ ለውጦችን እያመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለዚህም ቀን ከለሊት ሳይሉ የሚሰሩት የተቋሙ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና በከተማው ያሉ ኦፊሰሮች ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ሱሉም ተናግረዋል።

አክለውም ጊዜው የመረጃና ኮሙኒኬሽን እንደመሆኑ የስቱዲዮ ግንባታው የመረጃ ቅብብሎሽ የሚያሳድግና ተቋሙ የሚያከናውነውን ተግባራት ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረውና አጋዣ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል በማለት በቀጣይም በሙያዊና በቴክኖሎጂ በሚያስፈልጉ ነገሮች በሚቻላቸው ድጋፍ እንደሚያደረጉ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review