የመደመር መንግሥት ግቡ ሰርቶ ማሳካት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing የመደመር መንግሥት ግቡ ሰርቶ ማሳካት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

የመደመር መንግሥት ግቡ ሰርቶ ማሳካት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተጻፈው ”የመደመር መንግሥት” መጽሃፍ ለንባብ በቅቷል።

በመጽሐፍ የምረቃ መርሐ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ከዚህ ቀድም የለውጥ አራማጅነት የሚለካው ትናንትን በመናድ እና በማፍረስ እንጂ የጎደለን ሞልተን የላቀ የተሻለ አድርጎ አሸጋግሮ በመስጠት እንዳልነበር አስታውሰዋል።

ከዛ በተለየ የመደመር መንግስት ያልተሄደበትን መንገድ መጓዝ ይመርጣል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ለዚህም መነሾን መገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

‎አንዳንድ ሃገራት አሁን ያሉበት ሁኔታ የተከተሉት እና የመረጡት መንገድ አፍራሸ በመሆኑ እንደሆነ ጠቅሰው፤ እኛ ደግሞ በገንዘብም በሀሳብም በአሰራርም የሚገዝፈውን ህዳሴ ከነ ስብራቱ ተቀብለን በድል አጣቀናል ሲሉ ተናግረዋል።

‎ስኬት ባለቤቱ ብዙ መሆኑን አስረድተው የመደመር መንግስት እንዲህ ባለው ግዜ የሚመርጠው መንገድ ተሳክቷል፤ የስኬት ባለቤት እናንተ ሁኑ ነው የሚለው ሲሉ ተናግረዋል ።

‎ስኬት ለመሻማት የመደመር መንግስት ግዜ የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግቡ ሰርቶ ማሳካት ነው ብለዋል።

‎የመደመር መንግስት ሲያሳካም ብቻዬን ማሳካት እችላለሁ ብሎ እንደማያምን ገልፀው፤ ኢትዮጵያውያን በሚችሉት ሁሉ ተደምረው ያሳኩት የመላው ህዝብ ገድል እንጂ የአንድ መንግስት ወይም የግለሰብ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review