ከህመም ጋር ታግሎ ፈተናን በድል የተወጣው “አሉዲን”

You are currently viewing ከህመም ጋር ታግሎ ፈተናን በድል የተወጣው “አሉዲን”

‎AMN መስከረም 07/2018 ዓ/ም

‎ተማሪ አሉዲን ሁሴን የበደሌ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ታታሪ ተማሪ ነው።

‎የ12ኛ ከፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቆ የመፈተኛ ቀኑ ሲደርስ ሕመም ያጋጥመዋል ። ‎ተማሪ አሉዲን ህክምና ሂዶ ምርመራ ሲያደርግ የትርፍ አንጀት እንዳለበት በሀኪም ይነገረዋል።

‎በዚህ አጋጣሚ ጭንቀት ውስጥ የገባው አሉዲን ሕመሙ ፈተናውን መጨረስ የሚያስችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ት/ቤቱ ከሀኪሞች ጋር በመነጋገር መድኃኒት እየወሰደ እንዲፈተን መደረጉን የት/ቤቱ ር/መምህር አቶ ይልማ ገቢሳ የነበረውን ተናግረዋል። ህክምና እየተደረገለት ለ3 ቀን ሲሰጥ የነበረውን የማሕበራዊ ሳይንስ ፈተና ያጠናቀቀው ይህ ጎበዝ ተማሪ 472 ማምጣት ችሏል።

‎በወቅቱ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በበደሌ ኢፈ ቦሩ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ያለውን የፈተና ሂደት በጎበኙበት ወቅት ፣ ተማሪውን አበረታትተው እና መልካሙን ሁሉ ተመኝተው ነበር።

‎ሃገር የምትገነባው ፣ ችግርን ተቋቁመው ዓላማቸውን ለማሳካት በሚጥሩ እንደ አሉዲን ባሉ ብርቱ ዜጎች ጥረት ነው ማለታቸዉን ከጅማ ዩኒቨርስቲ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review