በመጭው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅት አብዛኛው ሰሜናዊና ስሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ተጠቆመ

You are currently viewing በመጭው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅት አብዛኛው ሰሜናዊና ስሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ተጠቆመ

AMN – መስከረም 8/2018 ዓ.ም

በመጭው የበጋ የአየር ጠባይ ወቅት አብዛኛው ሰሜናዊና ስሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ በተመለከተ ግምገማ እና የመጪውን የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ይፋ አድርጓል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢንስቲትዩቱ ግንቦት ላይ የሰጠው የክረምት 2017/18 የአየር ጠባይ ትንበያ መሬት ላይ ከተከሰተው ጋር የተጣጣመ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በመጭው በጋ በሚኖረው የአየር ጠባይ ወቅትም አብዛኛው ሰሜናዊና ስሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

መጭው የበጋ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ የሲዳማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛ ዝናብ የሚኖራቸው መሆኑን እንዲሁም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚያገኙ፣ በአንፃሩ የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡

በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎችም ከመደበኛ በላይ ሙቀት ሊከሰት እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን፣ የዘንድሮው የበጋ ወቅት በ2020/2021 ከነበረው የበጋ ወቅት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለውም ተመላክቷል።

ኢንስቲትዩቱ ህብረተሰቡ የሚሰጠውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ መግለጫዎች በቅርበት ክትትል በማድረግ ሊከሰት የሚችለውን የአደጋ ተጋላጭነትን በመቀነስ ስጋቶችን ወደ መልካም አጋጠሚዎች በመቀየር ምርትና ምርታማነትን ለማሰደግ የሚያሰችለውን እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም አሳስቧል።

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review