ከኢትዮጵያዊ እሴት ውጪ የሆኑ ባህሪያት በስፖርቱ መድረክ ሊኖሩ አይገባም ሲሉ አቶ በላይ ደጀን ተናገሩ

You are currently viewing ከኢትዮጵያዊ እሴት ውጪ የሆኑ ባህሪያት በስፖርቱ መድረክ ሊኖሩ አይገባም ሲሉ አቶ በላይ ደጀን ተናገሩ

AMN-መስከረም 08/2018 ዓ.ም

ከዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

በስታዲየም የሚስተዋሉ የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለቶችን ለማስተካከል ክለቦች ለደጋፊዎቻቸው ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸው ይታመናል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ከክለብ ደጋፊዎች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ በ2018 ዓ.ም በከተማዋ ደማቅ የእግር ኳስ ውድድር ይከናወናል ብለዋል።

ከኢትዮጵያዊ እሴት ውጪ የሆኑ ባህሪያት በስፖርቱ መድረክ ሊኖሩ አይገባም ያሉት ሃላፊው ቢሮው ከደጋፊ ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ምሁር ወገኔ ዋልተንጉስ (ዶ/ር) በሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለፃ ወደ ስታዲየም የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ ብቻ ሳይሆን ፣ ለመመልከት ብቻ የሚገቡ ተመልካቾች የሚስተናገዱበት መንገድ መዘርጋት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

ደጋፊዎች ከየክለቦቻቸው ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያሰፈነ አሰራር አለመኖሩ ተከትሎ ቅሬታዎች እና እንዲበረክቱ አድርጓል ብለዋል፡፡

በዚህ መንገድ መቀጠል ስፖርታዊ ጨዋነትን ማምጣት ስለማይቻል ክለቦች ተቋማዊ አደረጃጀት ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ ብቃት ባላቸው አመራሮች ሊመሩ ይገባል ሲሉ ወገኔ ዋልተንጉስ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

በዮናስ ሞላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review