ቀደምት አባቶች ጠላትን ድል እንደነሱት ሁሉ የዛሬው ትውልድም በታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢኮኖሚው ዘርፍ አሸናፊ መሆን እንደቻለ ተገለጸ

You are currently viewing ቀደምት አባቶች ጠላትን ድል እንደነሱት ሁሉ የዛሬው ትውልድም በታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢኮኖሚው ዘርፍ አሸናፊ መሆን እንደቻለ ተገለጸ

AMN – መስከረም 8/2018 ዓ.ም

ቀደምት አባቶች ጠላትን ድል እንደነሱት ሁሉ የዛሬው ትውልድም በታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢኮኖሚው ዘርፍ አሸናፊ መሆን እንደቻለ በአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረው ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የግድቡን መጠናቀቅ በማስመልከት 2 ሺህ የሚደርሱ ሴቶች በተገኙበት የፓናል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ ቀደምት አባቶች ጠላትን ድል እንደነሱት ሁሉ የዛሬው ትውልድም በታላቁ ህዳሴ ግድብ በኢኮኖሚው ዘርፍ አሸናፊ መሆን እንደሚቻል ያሳየበት ነው ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያንን የመቻል አቅም ያሳየ እና ኢትጵያውያን በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፈው በትብብር ገድል የሰሩበት ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በበኩላቸው፤ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቅሰው፤ ይህ የፓናል ውይይት ስለ አባይ የምንመክርበት ነው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ሴቶችም ህዳሴን በአንድነት እንደገነባነው ሁሉ ሌሎችንም ፕሮጀክቶች በህብረት ልንገነባ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review