ህዳሴ መጠናቀቅ ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ እንደሆነው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing ህዳሴ መጠናቀቅ ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ እንደሆነው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

AMN – መስከረም 8/2018 ዓ.ም

የህዳሴ መጠናቀቅ ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ እንደሆነው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገልፀዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት የምስክር ማህተም በሆነው አፋር ዛሬም የኢትዮጵያ ሰንደቅ በድል ሰልፍ ከፍ ብሎ መዋሉን ገልፀዋል፡፡

የአፋር መሬቱም ሰውም ለሃገር ሉዓላዊነት ዋጋ የከፈለ ጀግና ሆኖ ብቻ አይጠቀስም፤ የልማት ጮራ እየፈነጠቀበት ያለ የልማት አርበኞች ምድር ነው በማለት ገልፀዋል።

የህዳሴ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ልማት ለሚተጋው ለአፋር ሕዝብ ተጨማሪ ሃብት እና ወኔ ይሆነዋል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋፍ ሰልፉም የተስተጋባው የአፋር ሕዝብ ድምጽ ለልማት እና ሰላም የወገነ፣ የኢትዮጵያን ብሩህ ዘመን ዕውን ለማድረግ ያለመ እንደሆነ አይተናል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review