ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በ2018 በጀት ዓመት በላቀ ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ተናበውና ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር አሳሰቡ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ግብ ስምምነት ፊርማ መድረክ ተካሄዷል።

የከተማዋ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በ2018 በጀት ዓመት በላቀ ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ተናበውና ተቀናጅተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የዘንድሮው የከተማዋ እቅድ የለውጡ መንግስት የ10 አመት የልማት እቅድ አካል የሆነው የመጀመሪያው 5 አመት የመጨረሻው አመት የልማት እቅድ መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባኤዋ እቅዱን በተደመረ አቅም በመተግበር ከተማዋን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በትጋት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በእቅድ ግብ ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላት የሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና ተጠሪ ተቋማት ተገኝተዋል።
በምትኩ ተሾመ