የኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር 2018 ከመስከረም 18 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገለፀ

You are currently viewing የኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር 2018 ከመስከረም 18 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገለፀ

AMN – መስከረም 9/2018 ዓ.ም

የኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር 2018 ከመስከረም 18 እስከ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ኤግዚቢሽኑ እና ባዛሩን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከሀገሬ ኢቬንትና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደራራ ከተማ፤ የኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር 2018 ከመስከረም 18 – 23 /2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

በኤግዚቢሽኑ እና ባዛሩ የንግድ፣ የባህል አልባሳትና ጌጣጌጥ፣ የእጅ ሥራዎች እና የባህላዊ ምግቦች አውደ ርዕዮች እንደሚቀርቡ የሀገሬ ኢቬንትና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ ጥላሁን ጫላ ገልፀዋል።

በ2018 የኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር፤ ኢሬቻ የጋራ አንድነት እና ምልክት መሆኑን በሚያጎላ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በኤግዚቢሽኑ እና ባዛሩ የኦሮሞ ሕዝብና የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞችን ቱባ ባህል ከማክበር ባለፈ የተለያዩ የንግድ ትርኢቶች ይካሄዳሉ ተብሏል በመግለጫው።

ኤግዚቢሽኑና ባዛሩ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎች የሚፈጥር መሆኑንም በመግለጫው ተነስቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ የኢንዱስትሪ ቢሮ የዘርፍ ኃላፊ እና የበዓሉ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር)፤ በኤግዚቢሽኑ እና ባዛሩ ላይ ከበዓሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶች የሚቀርቡት በመሆኑ ህብረተሰቡ ምርቶችን ማስተዋወቅ፣ መሸጥ እና መግዛት ላይ እንዲሳተፍ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ በ11 ክፍለ ከተሞች የኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር እንደሚካሄድም ተገልጿል ።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review