የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የተካሄደበት እና ስኬታማ ውጤት የተመዘገበበት እንደነበር ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የተካሄደበት እና ስኬታማ ውጤት የተመዘገበበት እንደነበር ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – መስከረም 10/2018 ዓ.ም

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት የተካሄደበት እና ስኬታማ ውጤት የተመዘገበበት እንደነበር የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በተለይ የእንግሊዝኛ እና የሂሳብ ትምህርቶች ስትራቴጂ በአዲስ መልክ የተተገበረበትና እና የአመቱ የትምህርት አጀንዳ እንዲሆን የተደረገበት የትምህርት አመት እንደነበርም ዘላለም ሙላቱ (ደ/ር) አብራርተዋል፡፡

የትምህርት አመቱ ስኬታማ ውጤቶች የተመዘገቡበት፣ ልምድና ተሞክሮዎች የተወሰዱበት እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

በትምህርት አመራሩ ላይ የአቅም ግንባታ ስራ በተሳካ ሁኔታ የተሰራበት አመት እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በትምህርት ዘመኑ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎንም ጤናማ፣ የነቃ እና በአካል የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ስፖርታዊ ውድድሮች እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በየትምህርት ቤቱ የተካሄዱበትና ባህል እንዲሆኑ የተደረገበት መሆኑንም ሀላፊው አንስተዋል፡፡

በትምህርት ዘመኑ በተማሪዎች ምገባ፣ በትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት፣ በመጽሃፍ ስርጭት በኩልም በተሻለ ሁኔታ የቀረበበት እና በመማር ማስተማሩ ሂደትም በትክክል ድጋፍ የተደረገበት እንደነበርም ነው ሀላፊው ያብራሩት፡፡

ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) አክለውም፤ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የከተማ ግብርና ባህል እንዲሆንና የተማሪዎች እውቀትና ክህሎት እንዲጎለበት በሰርቶ ማሳያ ከማስተማር ባሻገር በምግብ ስርዓቱም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የተደረገበት አመት ነበር ብለዋል፡፡

እነዚህ ተግባራት በውጤታማነት በመሰራታቸው የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ሀላፊው፤ በተለይም የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍሎች የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን ተናግረዋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ፍጹም ሰላማዊ፣ ትምህርት ቤቶች ለማስተማሪያነት፣ መምህራን ለማስተማር እና ተማሪዎችም ለመማር ብቻ የተንሳቀሱበት እንደነበርም አመላክተዋል፡፡

በትምህርት ዘመኑ በትምህርት ቤቶች አካባቢዎች የነበሩ ለመማር ማስተማር እንቅፋት የሆኑ አዋኪ ድርጎቶችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት የተሰራበትና ውጤትም የተመዘገበበት እንደነበር ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ያስረዱት፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review