ባለፉት ቀናት የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች በመዲናዋ አዲስ አበባ ለጥበብ አፍቃሪያን ሲደርሱ ቆይተዋል፡፡ ዛሬን ጨምሮ በሚቀጥሉት ቀናትም መሰል መሰናዶዎች ይቀርባሉ። ከእነዚህ መካከል የሥዕል አውደ ርዕይ፣ የአዳዲስ መጽሐፍት ህትመት እና የመጽሐፍት ውይይት ይገኙበታል፡፡ ለመረጃ ይሆንዎት ዘንድ የአዲስ ልሳን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እንደሚከተለው አዘጋጅቷቸዋል፡፡
መጽሐፍት
“ካፌ ጎልጎታ” መጽሐፍት ለንባብ ሊበቃ ነው፡፡ በወጣቱ ደራሲ ይስሃቅ አብርሃም የተጻፈው ይህ መጽሐፍ፣ በቅድመ ህትመት ሽያጭ ዘዴ በማህበራዊ የትስስር ገጽ (ፌስቡክ) አማካይነት ለአንባብያን ቀርቧል፡፡ መጽሐፉ እውነተኛ ታሪክን ከምናባዊ ፈጠራ ጋር በማገናኘት የተጻፉ መጣጥፎችን የያዘ ነው፡፡ ደራሲው በማህበራዊ የትስስር ገጹ፤ “…ባለችኝ ትንሽ አቅም ስለ ትዝታ እና ተስፋ… ስለ ሞት እና ህይወት እያነሳሁ የተፈላሰፍኩት ካፌዎች ላይ በተደረደሩ በዛጉ ወርቃማ ወንበሮች ላይ ነበረ። …ከብላቴናነት ዘመን አንስቶ እግሬን ነክሳ ስላለቀቀች ኪነት አጎንብሼ ያለቀስኩት በእነዚህ ካፌዎች ውስጥ ነበረ! …እንግዲህ እነዚህን በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ፅሁፎች (ደብዳቤዎች፣ መጣጥፎች፣ ሂሶች፣ የፈጠራ ፅሁፎች) ሳይቀር ያሰብኳቸው፣ የፃፍኳቸው፣ የተብሰለሰልኩባቸው በእነዚህ ካፌዎች ውስጥ ነው” በማለት የመጽሐፉን ስያሜ ጭምር ለምን ካፌ ጎልጎታ እንደተባለ ጽፏል። መጽሐፉ በቅድመ ህትመት ሽያጭ ዘዴ ከወዲሁ በደራሲው በኩል መግዛት የሚቻል ሲሆን፤ የአንዱ መጽሐፍ ዋጋ 450 ብር ተተምኗል፡፡
በሌላ መረጃ ዛሬ ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ‘ምን ሆኛለሁ?’ እና ‘ኀልዮት’ በተሰኙ መጽሐፎች ላይ ውይይት ይደረጋል። ዛጎል የመጽሐፍት ባንክ ባሰናዳው በዚህ
የውይይት መርሃ ግብር የመጽሐፎቹ ደራሲዎች ትዕግሥት ዋልተንጉስ እና ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ በተጋባዥ እንግዳነት ይገኛሉ፡፡ የውይይት መርሃ ግበሩ አዘጋጅና አቅራቢ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ሲሆን፤ የሚካሄደው ደግሞ በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡ አድራሻው ቀበና፣ የካቶሊኮች ኪዳነ ምሕረት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ነጩ ሕንፃ አጠገብ ነው፡፡
በተያያዘ መረጃ ነገ “ስብሐቲዝም” የሀሳብ ውይይት ያደርጋል፡፡ “የነባርና አዲስ ሃሳቦች ግጭት” በሚል ርዕስ፣ የመነሻ ሃሳብ የሚያቀርበው የማህበረሰብ ሥነ ልቦና ባለሙያው ሱራፌል አየለ ነው፡፡ በውይይት መርሃ ግብሩ አዳዲስ እሳቤዎች ከተለምዷዊ አስተሳሰባችን ጋር የሚገቡበት ቅራኔ ይተነተናል ተብሏል። መርሃ ግብሩ የሚደረገው በብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ነው፡፡
ሥዕል
“የተመለሱ እይታዎች” አውደ ርዕይ ተከፈተ፡፡ የሠዓሊ ኪሩቤል ተፈሪ የሥዕል ስራዎች የቀረቡበት ይኸው አውደ ርዕይ ባሳለፍነው ሳምንት ረ?? ????? 7 ?? 2018 ?.????? ??? ???? ??? ??? ????? ???? ???? ???? ??? ???? ?? ????? ????? ????? ???? ???? ???? ?????? ??? ??? ??? ??? ???? 3 ?? 2018 ?.? ??? ???? ?????ዕቡ መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀ?? ??? ???? ??? ??? ????? ???? ???? ???? ??? ???? ?? ????? ????? ????? ???? ???? ???? ?????? ??? ??? ??? ??? ???? 3 ?? 2018 ?.? ??? ???? ?????ምሮ ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ውስጥ በዕይታ ላይ ይገኛል። የሰዓሊው የተለያዩ ጥበባዊ የፈጠራ ሥራዎች የቀረበበት አወደ ርዕዩ እስከ መጪው ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ቴአትር
በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ የተለያዩ ቴአትሮች ይታያሉ፡፡ ቅዳሜ 8:30 ሰዓት 12ቱ እንግዶች፣ 11፡30 ሰዓት ደግሞ ባሎችና ሚስቶች፣ እሁድ 8፡30 ሰዓት ንጉሥ አርማህ፣ እንዲሁም 11፡30 ሰዓት እምዩ ብረቷ ቴአትሮች በብሔራዊ ቴአትር ይታያሉ፡፡ የደመና ዳንኪረኞች የተሰኘው ቴአትር ደግሞ እሁድ በ8:00 ሰዓት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ይታያል።
በተጨማሪም ማክሰኞ በ11፡30 ሰዓት ሶስቱ አይጦች፣ ረዕቡ በ11፡30 ሰዓት የቅርብ ሩቅ፣ ሐሙስ 11:30 ሰዓት ሸምጋይ፣ አርብ በ11፡30 ሰዓት የሕይወት ታሪክ ቴአትሮች በብሔራዊ ቴአትር ለጥበብ አፍቃሪያን ለዕይታ ይቀርባሉ፡፡
በአብርሃም ገብሬ