በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

You are currently viewing በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

AMN – መስከረም 10/2018 ዓ.ም

በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በ46 የተለያዩ የሞያ አይነቶች ስልጠናቸውን በውጤታማነት ያጠናቀቁ 7 ሺህ 149 የቴክኒክና ሞያ ሰልጣኞችን በታላቅ ድምቀት መመረቃቸውን ገልፀዋል።

ለተመራቂዎችም እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ መልካም ምኞች አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት 2 ዓመታት በቴክኒክና ሞያ ስልጠና ዘርፍ ነባር ችግሮችን በመቅረፍ ለአገራዊ ብልፅግና የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲወጣ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት እያስመዘገብን እንገኛለን ብለዋል። በተለይም በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ ችለናል ሲሉም ገልፀዋል።

ሰልጣኞች በቆይታቸዉ 70 በመቶ የተግባር እንዲሁም 30 በመቶ የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉ ክህሎትን በማላቅ፣ ፈጠራን በመጨመር አበረታች ውጤት እያመጣ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

ለተመራቂዎችም፤ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት፤ ያለንበትን የውድድር ዓለም ከግምት በማስገባት ምንጊዜም ራሳችሁን በእውቀት፣ በክህሎት በተለይም በቴክኖሎጂ በማበልፀግ ፈጠራና ፍጥነትን የህይወታችሁ መርህ በማድረግ ስራ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅባቹሀል ሲሉም አስገንዝበዋል።

አስተዳደራችንም ይህን ለመደገፍ እንደ እስካሁኑ ሁሉ ከጎናችሁ መሆኑን ዳግም አረጋግጥላችኋለሁ ብለዋል።

መልካም የስራ ዘመን! በማለትም ከንቲባዋ ለተመራቂዎች መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review