የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ “ጊፋታ” በዓል እየተከበረ ይገኛል። “ጊፋታ” የወላይታ ሕዝብ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሻገርን የሚገልጽ የምስጋና በዓል ነው።
የጊፋታ በዓል አከባበር ለማሕበራዊ መስተጋብር ከሚሰጠው ፋይዳ በተጨማሪ በኢኮኖሚው መስክ የሚፈጥረው መነቃቃት ከፍተኛ እንደሆነም ይገለፃል ።

በበዓሉ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌደራልና ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ መሆኑን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ኤደን ንጉሴ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ገልፀዋል ።