የመደመር መንግሥት መፅሀፍ የዘመናት ችግሮችን የዳሰሰ እና መፍትሄ አመላካች መሆኑን በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ሙህራን ገልፀዋል።
የመደመር መንግሥት መፅሃፍ እሳቤ ላይ ያተኮረ ውይይት በየካ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል ።
የመደመር መንግሥት እሳቤ በተለያዩ ሙህራን ግንዛቤን የሚፉጥሩ የተለያዩ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተደርጓባቸዋል።
የውይይቱ አላማ የመደመር መንግሥት ዕሳቤን በማህበረሰቡ ለማፅረስ መሆኑን የተናገሩት የየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና፤ በቀጣይም ተመሳሳይ መርሃ ግብሮች በክፍለ ከተማው ይቀጥላሉ ብለዋል
የውይይቱ ተሳታፊዎቹ የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ለቀጣይ ትውልድ መሠረት የሚጥል እና ሀገርን በጋራ ለማሻገር የሚያግዝ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል
የመደመር መንግሥት መፅሀፍ ፍጥነትና ፈጠራን እንዲሁም ክፍተቶችን የማረም አቅም የሚፈጥር መሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።
በመርሃ ግብሩ የተለያዩ ሙህራን፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ፖለቲከኞችና ማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ሙህራን ተሳትፈዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ