የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ወጣቶች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡
በበዓላቱ አከባበር ዙሪያ በብሎክ፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ውይይት የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፤ መስቀል የእርቅ፣ የፍቅር እና የሰላም ምልክት ነው ብለዋል፡፡
መስቀል አንድነታችንን የሚያሳይ፣ አብሮነታችንን የሚያጎላ፣ የመደመርን ጥቅም በጉልህ የሚያስረዳ በመሆኑ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ የሚከበር እና ደምቀን የምንታይበት ቅርሳችን ነው ብለዋል።
ሀላፊው አክለውም፤ መስቀል የተራራቁ የሚቀራረቡበት፣ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ጥላቻ በፍቅር፣ ሞት በሕይወት፣ ጨለማ በብርሃን የሚተካበት ዓመቱን ሙሉ በሰላም ለመኖር የሚያስችል ብርሃን የሚለኮስበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

መስቀል በዓለም የትምህርት ሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በቅርስነት እንደመመዝገቡ መጠን በርካታ የውጭ እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጎብኚዎች በስፋት የሚታደሙበት በመሆኑ በተለመደው እንግዳ ተቀባይነት ማስተናገድ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን ላሸጋገረው ፈጣሪ እና በፈጣሪ ፍቃድ የሞላው ውሃ ጎድሎ ከዘመድ አዝማድ በመገናኘቱ ሐሴት የሚያደርግበት እና ሰው የፈጠረውን ፈጣሪ አመስጋኝ መሆኑን የሚያሳይበት ተናፋቂ በዓል ስለመሆኑም የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።
ኢሬቻ፤ የምስጋና ቀን የይቅርታ በዓል ነው፤ ዓመቱን በምስጋና፣ በፍቅር እና በዕርቅ ጀምረን እንድንጨርስ መልካም የሆነውን ሁሉ እንድናደርግ በዓሉ ትልቅ ትምህርት ይሰጠናልም ነው ያሉት፡፡
ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል፣ በሀይማኖት ሳይለያይ፣ በፖለቲካ ሳይነጣጠል በሁሉም ኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ከብረት በጠነከረ አንድነት ካለምንም ልዩነት የሚከበር የአብሮነት መገለጫ በዓል መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ኢሬቻ ሲከበር እርቅ ማድረግ መሰረታዊ እንደመሆኑ መጠን የተቀያየመ ይቅር በመባባል እንዲያከብር የገዳ ሥርዓት ያዛልም ነው ያሉት።
ኢሬቻ ከኢትዮጵያዊያንም አልፎ የዓለም ሀብት የሆነው የገዳ ስርዓት አካል በመሆኑ፣ ቱሪስቶች የሚጎርፉበት፤ የመጪውን ዘመን ደስታ በጋራ የምናጣጥምበት፣ ለሰላማችን በጋራ የምንሰለፍበት፣ የአንድነታችን ተምሳሌት ስለሆነ፤ በዓሉን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን የከተማችን ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች