የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና ኃይማኖታዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና ኃይማኖታዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ
  • Post category:በዓል

AMN – መስከረም 12/2018 ዓ.ም

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና ኃይማኖታዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው በበአላቱ አከባበር ዙሪያ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተወጣጡ የህብረተሰብ ትወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሚደግሳ ከበደ፤ በአላቱ ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው በስኬት እንዲከበሩ በጸጥታው ዘርፍ ህዝብን ባሳተፈ አግባብ ሙሉ ዝግጅት መደረጉን አስታዉቀዋል።

በአላቱ የህዝብና የኢትዮጵያ ውበትና ጸጋ ናቸው ያሉት አቶ ሚደግሳ፤ ሙሉ ስነሥርአታቸው የኃይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች በሚያስቀምጡት አግባብ ይከበራሉ ብለዋል።

ያልተፈቀዱ እና የማይገባ መልእክቶችና ምልክቶች የተከለከሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በአላቱን ምክንያት በማድረግ በቁሳቁሶችና የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይፈቀድና ይልቁንም የኢትዮጵያን ምርት ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል።

ህብረተሰቡ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅም አቶ ሚደግሳ አሳስበዋል፡፡

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review