በበዓላቱ ለመታደም የሚመጡ እንግዶች ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዶ ተስተናግደው እንዲመለሱ ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing በበዓላቱ ለመታደም የሚመጡ እንግዶች ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዶ ተስተናግደው እንዲመለሱ ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ

AMN – መስከረም 12/2018 ዓ.ም

የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላትን ለመታደም የሚመጡ እንግዶች ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዶ ተስተናግደው እንዲመለሱ ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከሸገር ሲቲ ክፍለ ከተሞች የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ወጣቶችጋር በበአላቱ አከባበር ዙሪያ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

የመተሳሰብ፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት የሆኑት የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከማድረግም ባሻገር፤ በዓላቱን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዶ ተስተናግደው እንዲመለሱ ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ገልጸዋል፡፡

በዓላቱ የኢትዮጵያዊያንን ትንሳኤ የሚያረጋግጠው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ማግስት መከበራቸው የተለየ ያደርገዋል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ በድል ማግስት የሚከበሩት እነዚህ በዓላት የኢትዮጵያን ገፅታም ጭምር የምናስተዋውቅባቸው ናቸው ብለዋል፡፡

በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል እና ከገዳ ስርአት የተቀዳው ኢሬቻ በዓል፣ የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የዓለምም ሀብት ናቸው ያሉት አቶ አድማሱ ደቻሳ፤ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከተቀረው ዓለም በዓሉን ለመታደም ወደ መዲናዋ ለሚተሙ ዜጎች፣ በመዲናዋ ገፅታ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ እንግዳ ተቀባይነትም ጭምር እንዲደሰቱ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review