የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
ሀሠተኛ ሠነዶችን ማዘጋጀት፣ ማሠራጨትና መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ህገ ወጥ ድርጊት የሚገቡ ግለሠቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየተደረገም ይገኛል ብሏል።
በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጎማ ቁጠባ ፖሊስ ጣቢያ በክፍለ ከተማው ወረዳ 7 ቀጠና 1 አካባቢ ሀሠተኛ ሠነዶችን በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ የወንጀለኞች ጥናት ሲያደርግ ቆይቶ፣ የፍርድ ቤት የቤት መበርበሪያና የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ፡-
ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ፣
ፖስፖርት፣ የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎች፣
የ10ኛና የ12ኛ መልቀቂያ
የትግራይ ክልል መታወቂያ
የአማራ ክልል መታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ፣
የተሽከርካሪ ቦሎ፣
የተለያዩ ሪሲቶች፣
የልደት ካርድ፣
ሊሰራ የተዘጋጀ የአዲስ አበባ መታወቂያ፣
የፖለቲካ ጥገኝነት ለሚጠይቁ ግለሰቦች የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
ሠነዶች ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸው፦
1018 የተለያዩ ማህተሞች፣
1 ፕሪተር፣
1 ህትመት ማሽን፣
2 ላፕቶፕ ፣
2 ስካነር፣
1አጉሊ መነፅር፣
2 ማሸጊያ ማሽን፣
8 ሲዲዎች፣
1 መጠረዣ፣
1የፖስፖርት ማሽን፣
11የማህተም መርገጫ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል።
ህብረተሠቡ ሀሰተኛ ሰነዶችን መጠቀም በሀገር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛና ትውልድ ገዳይ መሆኑን ተረድቶ፣ መሠል ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ተሳትፎውን እንዲያጎለብት የአዲሰ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ፣ ተቋማትም ሠራተኞችን በሚቀጥሩበት ወቅት የተቀጣሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸው ላይ ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርጉም ጠቅላይ መምሪያው አሳስቧል፡፡