የመስቀልና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የበኩላቸዉን ድርሻ እንደሚወጡ የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

You are currently viewing የመስቀልና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የበኩላቸዉን ድርሻ እንደሚወጡ የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ
  • Post category:በዓል

AMN መስከረም 12/2018

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር : የመልካ ፉሪና መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማዎች የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸዉን ተጠብቀዉ እንዲከበሩ የሚያስችል ውይይት አካሄደዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የዘንድሮ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ስናከብር የዘመናት ጥያቄ የነበረዉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጠናቀቀበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የመስቀል እና የኢሬቻ በአላት ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መንገድ እንዲከበር ከሸገር ክፍለ ከተሞች ጋር በትብብር እንየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ በበኩላቸዉ የመስቀልና የኢሬቻ በአላት በርካታ ህዝብ የሚታደምባቸው መሆኑን ገልፀው እነዚህ በአላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ የክፍለ ከተሞቹ ነዋሪዎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

በተለይም ወጣቶች ለፀጥታ አካላት ታዛዥና አጋዥ መሆን፣ የተከለከሉ ነገሮችን ባለመጠቀም የየራሳቸዉን ሚና መወጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ገለቱ ሁለቱም በአላት በርካታ ህዝቦች ወጥተው በአንድነት የሚያከብራቸው ሲሆኑ ባህላዊ ሀይማኖታዊ እሴቶቻቸው ተጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ በጋራ እንደሚሰራ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review