ውጤት ያጣነው በስልጠናችን ምክንያት ነው ሲል ኮማንደር ስለሺ ስህን ተናገረ

You are currently viewing ውጤት ያጣነው በስልጠናችን ምክንያት ነው ሲል ኮማንደር ስለሺ ስህን ተናገረ

AMN – መስከረም 13/2018 ዓ.ም

በ20ኛው የቶኪዮ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ልዑኩ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሌሎች የስፖርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች አቀባበል አድርገዋል፡፡

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን፤ ውጤት ያጣነው በስልጠናችን ምክንያት ነው ብሏል፡፡

ባለፉት ስምንት ዓመታት አትሌቶች በቂ እገዛ አላገኙም ያለው ፕሬዝዳንቱ፤ ውድድሩ ክፍተቶቻችንን እንድናይ አግዞናል ሲል ተናግሯል፡፡

በተለይ በስልጠናው ወደ ኋላ መቅረታችን ውጤት ለማጣታችን እንደ ትልቅ ምክንያት ይጠቀሳል ሲል በንግግሩ ጠቁሟል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረውን ስራ አስፈፃሚ አካሄድ ተከትለን በመሄዳችን የታየው ውጤት ተመዝግቧል ያለው ኮማንደር ስለሺ፤ እርሱ በፕሬዝዳንትነት የሚመራው አዲሱ ስራ አስፈፃሚ የተሻሉ ስራዎችን ሰርቶ ሕዝቡን ለመካስ እንደተዘጋጀ አብራርቷል፡፡

ኮማንደር ስለሺ ስህን በቀጣይ አትሌቲክሱን ወደ ነበረበት የሚመልሱ ስራዎችን ሰርተን ለሕዝቡ ይፋ እናደርጋለን ሲልም ቃል ገብቷል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review