የጋሞዎች “ዮ ማስቃላ”፣ የዘይሴዎች “ቡዶ ኬሶ” እና የጊድቾዎች “ባላ ካዳቤ” በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው

You are currently viewing የጋሞዎች “ዮ ማስቃላ”፣ የዘይሴዎች “ቡዶ ኬሶ” እና የጊድቾዎች “ባላ ካዳቤ” በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው

AMN – መስከረም 13/2018 ዓ.ም

የጋሞዎች “ዮ ማስቃላ”፣ የዘይሴዎች “ቡዶ ኬሶ” እና የጊድቾዎች “ባላ ካዳቤ” የ2018 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል በተለያዩ ትእይንቶች በአርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሽዊት ሻንካ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) እና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲ እናሌሎች የክልልና የፌዴራል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የጋሞ ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች በመከበር ላይ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዓሉ አብሮነትና አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች ነው እየተከበረ ነው።

በተጨማሪም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች፣ የጋሞ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች በመታደም ላይ ይገኛሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review