የ2018 የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው ይከበሩ ዘንድ ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ተመላከተ፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ከተማ አጎራባች ክፍለ ከተሞች ከሆኑት ቡራዩ ክፍለ ከተማ ጋር በመሆን ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀትና ትውፊታቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ የሚያስችል የህዝብ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በአላቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለአለም የምናሳይባቸው ናቸው ብለዋል።
በዓላቱ የኢትዮጵያውያንን ትንሳኤ የሚያረጋግጠው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ማግስት መከበራቸው ልዩ ስሜት አለው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ በድል ማግስት የሚከበሩ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ገፅታ ጭምር ለማስተዋወቅ ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በዓላቱን የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት እና አብሮነት በማሳየት ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ በድምቀት ለማክበር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በመሀመድኑር አሊ