በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሦስተኛ ዙር ውድድር ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሳውዛምፕተንን አስተናግዶ 2ለ1 አሸንፏል።
ለሊቨርፑል አሌክሳንደር ኢዛክ እና ሁጎ ኢኪቲኬ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል። በጨዋታው ኢኪቲኬ ግብ አስቆጥሮ መለያውን በማውለቁ ሁለተኛ ቢጫ ተመልክቶ ከሜዳ ወጥቷል።
ቼልሲ የሊግ ዋን ተወዳዳሪው ሊንኮልን ሲቲን 2ለ1 ረቷል። ቀድሞ ግብ የተቆጠረበት ቼልሲ በታሪክ ጆርጅ እና ፋኩንዶ ቦናኖቴ ግቦች አራተኛ ዙሩን ተቀላቅሏል።
በጨዋታው ኢንዞ ማሬስካ አሌሃንድሮ ጋርናቾን የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ አካቶ አጫውቷል። በሌሎች ጨዋታዎች ብራይተን ከሜዳው ውጪ ባርንስሌይን 6ለ0 ሲረታ ፤ በርንሌይ በሜዳው በካርዲፍ ሲቲ 2ለ1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። በፕሪምየር ሊጉ አምስቱንም ጨዋታዎች የተሸነፈው ወልቭስ ኤቨርተንን 2ለ0 አሸንፎ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።
ፉልሃም ካምብሪጅ ዩናይትድን 1ለ0 በማሸነፍ አራተኛ ዙሩን የተቀላቀለ ሌላኛው ክለብ ሆኗል።
በሸዋንግዛው ግርማ