የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር የመርካቶ ገበያ ነጋዴዎች ገለፁ

You are currently viewing የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር የመርካቶ ገበያ ነጋዴዎች ገለፁ

AMN – መስከረም 14/2018 ዓ.ም

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር የመርካቶ ገበያ ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡

ነጋዴዎቹ በማንኛውም ጊዜ ከአገሪቱ የልማት ስራዎች ጎን ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በመርካቶ ገበያ ከሚገኙ ነጋዴዎች ጋር ባደረገው ቆይታ፤ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላለፉት አስራ አራት አመታት ቦንድ በመግዛትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የድርሻቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ነጋደዎቹ ተናግረዋል።

የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅን በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር የገልጹት ነጋዴዎቹ፤ ከእነሱ የተሰበሰበው ግብር እና ሌሎች ገቢዎች ለሀገርና ለትውልድ ጠቃሚ ለሆነው ለዚህ ፕሮጀክት በማዋሉ ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው እና እኛ እራሳችንን ችለን በራሳችን አቅም የሰራነው ይህ ፕሮጀክት፤ የኢትዮጵያን እድገት አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ እንደሆነና ለአፍሪካውያን ኩራት መሆኑንም ተናግረዋል።

በቀጣይም ሀገሪቱ ያቀደቻቸውን የልማት ስራዎች ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያጣችውን የባህር በርም መልሶ ለማግኘት መንግስት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በደረጀ በየነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review