የመደመር መንግሥት መጽሐፍ መደመር ለሀገር ልማትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን ያመላከተ መሆኑን ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ገለፁ

You are currently viewing የመደመር መንግሥት መጽሐፍ መደመር ለሀገር ልማትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን ያመላከተ መሆኑን ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ገለፁ

AMN – መስከረም 14/2018 ዓ.ም

የመደመር መንግሥት መጽሐፍ መደመር ለሀገር ዘላቂ ልማትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን ያመላከተ ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተጻፈው አራተኛው የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) በውይይቱ ወቅት ባነሱት ሀሳብ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መደመር በሚል ርዕስ ባሳተሟቸው አራት መጻሕፍት በርካታ ቁልፍ ሃሳቦች ጎልተው ይነሳሉ ብለዋል።

እነዚህ መጻሕፍት በዋናነት በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት፣ አንድነትና ብልጽግና ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ለሀገር ዘላቂ ልማት፣ አንድነትና ብልፅግና መደመር አስፈላጊ እና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በአንክሮ ያነሳል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በርካታ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና ብሔረሰቦች እንዳሏት አመልክተው፤ ይህን እንዴት በጥንካሬ መጠቀም እንደሚቻል መጽሐፉ ማስቀመጡንም መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መደመር እንደመፍትሄ ሃሳብ፣ ልዩነቶችን በማስታረቅ፣ አንድነትና ብሔራዊ ማንነትን በማጠናከር ጠንካራ ሀገር መገንባት በአራቱም መጻሕፍት ውስጥ ጎልተው የሚነሱ ሃሳቦች ናቸው ብለዋል።

መደመር ሀገር በቀል እሳቤ ለሀገረ-መንግስት ግንባታ መሰረት እንደሆነ በግልፅ እንደሚያስቀምጥም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

የኪንግ ኦፍ አባይ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ኡስታዝ ጀማል በሽር የመደመር መንግሥት መጽሐፍ አብሮነትና መተባበር ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ያነሳል ብለዋል።

የመደመር ሃሳብ ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም አስፈላጊ እና ወሳኝ መሆኑንም ነው ኡስታዝ ጀማል የተናገሩት።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌታሁን አበራ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት መጽሐፍ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በሌሎች ወሳኝ ዘርፎች ሀገርን እንዴት ማሻገር እንደሚቻል የሚያመላክት ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review